ለጥያቄዎቻችሁ መልስ!

አንድ ተከታታያችን “የኢትዮጵያን ባንዲራ ሲያቃጥሉ የነበሩት 3 የቤት ሰራተኞች ሳይታሰብ በተቀጣጠለው እሳት ሶስቱም ሴቶች እና አንድ አራስ ህፃን ልጅ ህይወታቸው አለፈ ሲል BBC News ዘግቧል፣ ይህን አጣሩልን” ብሎ ጥያቄ ለኢትዮጵያ ቼክ አቅርቧል፣ ከጥያቄው ጋር የተያያዘው ምስልም ከታች ይታያል።

ኢትዮጵያ ቼክ Fotoforensics በመጠቀም ባደረገው ማጣራት በእንግሊዘኛ እንደ አርዕስት የተፃፈው እና ‘በእሳት ተቃጥለው ሰዎች ሞቱ’ የሚለው ፅሁፍ የፎቶሾፕ ቅንብር መሆኑን ደርሶበታል፣ ቅንብር መሆኑን የሚያሳየውን ምስል ከውጤቱ መመልከት ይቻላል። በተጨማሪም ቢቢሲ እንዲህ አይነት ዜና እንዳልፃፈ ድረ-ገፁ ላይ ገብተን መመልከት ችለናል።

ይሁንና ስክሪንሾቱ የተወሰደው በፌስቡክ ከተሰራጨ ቪድዮ ሲሆን ይህም ባንዲራ የማቃጠል ድርጊት ትክክለኛ ቪድዮ መሆኑን ተመልክተናል።

ስለዚህ በኢትዮጵያ ቼክ የምርመራ ውጤት መሰረት ቢቢሲ ሰራው የተባለው ዜና የተሳሳተ ሲሆን የስክሪንሾት ምስሉ የተወሰደበት ቪድዮ ግን ትክክለኛ ነው።

ወቅታዊ መረጃዎችን ቀጥታ በኢሜልዎ ለማግኘት ይመዝገቡ

    ያቀረቡትን የግል መረጃ በግላዊ መመሪያችን መሠረት እንጠብቃለን::