በትግራይ ክልል አንዳንድ ቦታዎች የስልክ አገልግሎት በድጋሜ የተቋረጠበት ምክንያት ምንድን ነው?

ትናንት ከሰአት በሗላ ጀምሮ በትግራይ ክልል አንዳንድ አካባቢዎች የስልክ አገልግሎት እንደገና ስለመቋረጡ የሚገልጹ መረጃዎች በማህበራዊ ሚዲያ ላይ ተሰራጭተዋል።

መረጃው ትክክል መሆኑን የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ስራ አስፈጻሚ ወይዘሪት ፍሬሕይወት ታምሩ ለኢትዮጵያ ቼክ አረጋግጠዋል።

ዋና ስራ አስፈጻሚዋ እንደተናገሩት የስልክ አገልግሎቱ የተቋረጠው በመቀሌ እና በአዲሽሁ ከተማ መካከል የሚገኝ የፋይበር መስመር በመቆረጡ ምክንያት ሲሆን አገልግሎቱን እንደገና ለማስጀምረ ወደ ስፍራው የተላኩ ሶስት ቡድኖች ዛሬ ከማለዳው ጀምሮ የጥገና ስራ በማከናወን ላይ ይገኛሉ።

በቶሎ የደህንነት ከለላ (security clearance) አለማግኘት፣ ከዚህ በፊት በክልሉ የቴሌኮም መሰረተ ልማት የደረሰው ከፍተኛ ጉዳት እንዲሁም የሀይል አቅርቦት ጥገናውን በፍጥነት ለማከናወን የገጠሙ ተግዳሮቶች እንደሆኑ ዋና ስራ አስፈጻሚዋ ጨምረው ለኢትዮጵያ ቼክ ገልጸዋል።

Update: ተቋርጦ የነበረው የስልክ አገልግሎት አሁን መስራት መጀመሩ ታውቋል።

ወቅታዊ መረጃዎችን ቀጥታ በኢሜልዎ ለማግኘት ይመዝገቡ

    ያቀረቡትን የግል መረጃ በግላዊ መመሪያችን መሠረት እንጠብቃለን::