በማህበራዊ ሚድያ ላይ ስለ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድን ደህንነት የተናፈሰው ወሬ ምንድን ነው?
“የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድን ደህንነት አስመልክቶ በማኅበራዊ ሚዲያ የሚናፈሰው ወሬ የሀሰት እንደ ሆነ ሁሉም ሰው እንዲገነዘብ ለማሳሰብ እንወዳለን” በማለት የጠ/ሚር ፅ/ቤት ከደቂቃዎች በፊት አስታውቋል።
ፅ/ቤቱ መግለጫውን ያወጣው በማህበራዊ ሚድያ ላይ ጠ/ሚሩ ጉዳት እንዳጋጠማቸው እና ለህክምና ወደ ውጭ ሀገር እንደሄዱ የሚገልፅ ፅሁፍ መውጣቱን ተከትሎ ነው።
ኢትዮጵያ ቼክ ባለፈው አንድ ሰአት ውስጥ ከተጨማሪ ሁለት ምንጮች ማረጋገጥ እንደቻለው የተሰራጨው መረጃው ፍፁም ውሸት ነው፣ ጠ/ሚሩም መደበኛ ስራቸው ላይ ይገኛሉ። ይህን መረጃ በመጀመርያ ያሰራጨ ግለሰብም ፅሁፎቹን አሁን አጥፍቷል።
የህብረተሰቡን ሰላም እና መረጋጋት የሚያውኩ እና ሀሰተኛ መረጃዎችን ባለማጋራት ሀላፊነታችንን እንወጣ።
ወቅታዊ መረጃዎችን ቀጥታ በኢሜልዎ ለማግኘት ይመዝገቡ
ያቀረቡትን የግል መረጃ በግላዊ መመሪያችን መሠረት እንጠብቃለን::