“የትግራይ ክልል ዎና ስራ አስፈጻሚ ዶ/ር ሙሉ ነጋ የስልጣን መልቀቂያ ደብዳቤ አስገብተዋል?”
“መልቀቂያ አላስገባሁም፣ ስራዬን በመስራት ላይ እገኛለሁ!”– ዶክተር ሙሉ ነጋ
የትግራይ ክልል ዋና ሥራ አስፈጻሚ ዶ/ር ሙሉ ነጋ የስልጣን መልቀቂያ ደብዳቤ ለጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት አስገብተዋል የሚል ፅሁፍ በተለይ ትዊተር ላይ እየተሰራጨ ይገኛል።
ኢትዮጵያ ቼክ ስለመረጃው ትክክለኛነት ለማጣራት ዶክተር ሙሉን ያናገረ ሲሆን “ሀሰት ነው” የሚል ምላሽ አግኝቷል። ዶክተር ሙሉ “የተሰራጨው መረጃ ሀሰተኛ ነው፣ መልቀቂያ አላስገባሁም፣ ስራዬን በመስራት ላይ እገኛለሁ” ሲሉ ለኢትዮጵያ ቼክ አስረድተዋል።
አንድ ስማቸው እንዳይጠቀስ የፈለጉ የፌደራል መንግስት ባለስልጣንም “ይህ ነጭ ውሸት ነው፣ እንዲህ አይነት የሀሰት ወሬ በተወራ ቁጥር መልስ መስጠት ያስቸግረናል” ብለዋል።
ወቅታዊ መረጃዎችን ቀጥታ በኢሜልዎ ለማግኘት ይመዝገቡ
ያቀረቡትን የግል መረጃ በግላዊ መመሪያችን መሠረት እንጠብቃለን::