የአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ የንግድ ቀጠና እንቅስቃሴውን እንዲሁም መቀመጫውን ከኢትዮጵያ ወደ ጋና አዙሯል?

“Ghana Stories” የተባለ የትዊተር አካውንት የአፍሪካ ህብረት ከአጉራዊ የንግድ ቀጠና ጋር የተያያዘ እንቅስቃሴውን ከኢትዮጵያ ወደ ጋና እንዳዞረ አስነብቧል፣ በርካቶችም መረጃውን አጋርተውታል። በዚህም መሰረት ጋና ተጠቃሚ እንደምትሆን ተገልጿል።

ኢትዮጵያ ቼክ ከአፍሪካ ህብረት በዚህ ዙርያ ማብራርያ የጠየቀ ሲሆን መረጃው ትክክል እንዳልሆነ ለመረዳት ተችሏል።

የህብረቱ የመረጃ ክፍል ሀላፊ ኤስቴር አዛ-ታንኮው “በ13ኛው የመሪዎች ጉባኤ የቀጠናው ሴክሬተርያት መቀመጫ በጋና እንዲሆን ተወስኖ ከጃንዋሪ 1 ጀምሮ ስራውን ጀምሯል። በውሳኔው መሰረት ጋና እንዲሆን ተደረገ እንጂ ከኢትዮጵያ አልዞረም፣ ይህም ማለት ኢትዮጵያ ከመጀመርያውም መቀመጫ አልነበረችም” ብለው ለኢትዮጵያ ቼክ አብራርተዋል።

በተጨማሪም ከአፍሪካ ህብረት የንግድ እና ኢንደስትሪ ኮሚሽን ያገኘነው መረጃ እንደሚያሳየው በኢትዮጵያ ሲካሄድ የነበረው ቀጠናውን የመመስረት ውይይት እንጂ ቀጠናው በኢትዮጵያ መስሪያ ቤቱን እንዲያቋቁም አልነበረም።

ወቅታዊ መረጃዎችን ቀጥታ በኢሜልዎ ለማግኘት ይመዝገቡ

    ያቀረቡትን የግል መረጃ በግላዊ መመሪያችን መሠረት እንጠብቃለን::