ይህ በፕሮፌሰር መረራ ስም እና ፎቶ የተከፈተ አካውንት በእርግጥ የእርሳቸው ነው?
ይህ የፕሮፌሰር መራራ ጉዲና ስምን እና ፎቶን በመጠቀም የተከፈተ የትዊተር አካውንት የእርሳቸው አለመሆኑን ፕሮፌሰር መረራ ለኢትዮጵያ ቼክ አረጋግጠዋል።
ብዙ ሺህ ተከታይ ያላቸው ተጽዕኖ ፈጣሪ ግለሰቦች በአካውንቱ የሚተላለፉ መልዕክቶች የፕሮፌሰር መረራ መሆናቸውን በመጥቀስ ሲያጋሩ ተመልክተናል። እንደዚህ አይነት አስመስለው የተከፈቱ አካውንቶችን የሚከታተሉ ከሆነ ለሀሰተኛ መረጃ እንዳይጋለጡ ጊዜ ሳያጠፉ መከተል እንዲያቆሙ እንመክራለን።
Note: ከዚህ በፊት ተከፍቶ የነበረው የፕሮ መረራ አካውንትና ይህ የተለያዩ ናቸው።
ወቅታዊ መረጃዎችን ቀጥታ በኢሜልዎ ለማግኘት ይመዝገቡ
ያቀረቡትን የግል መረጃ በግላዊ መመሪያችን መሠረት እንጠብቃለን::