በኤርትራ አሻ ጎልጎል ተከማችተው የሚታዩት ተሽከርካሪዎች ከትግራይ ክልል ተሰርቀው የተወሰዱ ናቸው?
በኤርትራ አሻ ጎልጎል ተከማችተው የሚታዩት ተሽከርካሪዎች ከትግራይ ክልል ተሰርቀው የተወሰዱ ናቸው?
በርካታ የፌስቡክ ገጾች እና የትዊተር አካውንቶች ከትግራይ ክልል የተሰረቁ ተሽከርካሪዎች በኤርትራ በሚገኝ አሻ ጎልጎል በተባለ ቦታ መከማቸታቸውን ያሳያሉ ያሏቸውን የሳተላይት ምስሎች አሰራጭተዋል።
ከኤርትራ ዋና ከተማ አስመራ በስተደቡብ 36 ኪሎሜትር ርቀት ላይ በሚገኘው በዚህ ቦታ ብዛት ያላቸው ተሽከርካሪዎች ተከማችተው እንደሚገኙ ጎግል ኧርዝ ያሳያል።
በተያያዘው ምስል ላይ እንዲሁም በጎግል ኧርዝ መረጃ መሰረት የሳተላይት ምስሎቹ የተወሰዱት እ.አ.አ አፕሪል 2019 ላይ ነው። ይህም የፌዴራል መንግስት በትግራይ ክልል “የህግ ማስከበር ዘመቻ” ያለውን እርምጃ መውሰድ ከመጀመሩ ከ1 ዓመት ከ8 ወር በፊት ሲሆን ይህም ከወቅቱ የትግራይ ሁኔታ ጋር ግንኙነት እንደሌለው ያረጋግጣል።
የምስሎቹ ጉዳይ እውነታው ይህ ቢሆንም ተፈፀመ የተባለ ዝርፊያ በብዙ ሰዎች ሲነገር ይሰማል፣ ኢትዮጵያ ቼክ በዚህም ዙርያ ማጣራት በማድረግ መረጃ ለማድረስ ጥረት ያረጋል።
ወቅታዊ መረጃዎችን ቀጥታ በኢሜልዎ ለማግኘት ይመዝገቡ
ያቀረቡትን የግል መረጃ በግላዊ መመሪያችን መሠረት እንጠብቃለን::